መጽሀፍ ቅዱስ በክርስትና ውስጥ የእምነት መጽሀፍ ብቻ ሳይሆን
የህይወት መንገድን የሚያስተምር እስትንፋሰ እ/ር ያለበት የህይወት ቃልም ጭምር ነው፡፡
መጸሀፍ ቅዱስ በክርስትና ውስጥ ያለውን የገዘፈ ምስል ያህል
እጅግ ብዙ ጥያቄዎች መጸሀፉን ለማጣጣል ይነሳሉ፡፡ በርግጥ ሁሉም ጥያቄዎች መ/ቅዱስን ለማጣጣል ነው ማለትም ተገቢ ዐይሆንም፡፡
ምክኒያቱም የሚነሱትን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ ካልተቻለ ስህተቱ የሚሆነው የክርስቲያኖች ይሆናል፡፡
በዚህ አጭር ፅሁፍ ውስጥ በመጀመሪያ በአጭሩ ስለ መፀሀፍ ቅዱስ
በማባራራት ፤ በመፅሀፍ ቅዱስላይ የሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎችን ለመመለስ እሞክራለሁ፡፡
I. መፀሀፍ
ቅዱስ
መፀሀፍ ቅዱስ በይሁዲዎች እና በክርስቲያኖች ሀይማኖት ውስጥ የተከበረ
መጸሀፍ ሲሆን በይሁዲዎች ከጅምሩ በእብራይስጥ የተፃፉ 39 መጸሀፍትን የሚያካትት ሲሆን በክርስቲያኖች ግን ትንሽ ለየት ያለ ነው፡፡
በዋናነት በሁለት የተከፈለ ነው( በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን)፡፡ የአዲስ ኪዳን መጸሀፍት 27 ሲሆኑ የብሉይ ኪዳን መፀሀፍት ደግሞ
39 ናቸው፡፡ በተጨማሪም 15 የሚጠጉ አፖክሪፋ መጸሀፍትን በተለያዩ የክርስቲያን አካላት በተጨማሪነት ያካትታሉ፡፡ የተወሰኑት የአፖክሪፋ
መጸሀፍትና 27ቱ የአዲስ ኪዳን መጸሀፍት በቀዳሚነት በግሪክ ቋንቋ ተጻፉ ሲሆን የብሉይ ኪዳን መጸሀፍት ግን በእብራይስጥ ነው የተፃፈው፡፡
መጸሀፍ ቅዱስ ከ1400 አመታት በላይ በፈጀ
ጊዜ እና ከ40 በሚልቁ ጸሀፍት የተጻፈሲሆን በይዘቱም ፡-
®
የታሪክ መጸሀፍት (22)
- የብሉይ ኪዳን 17
- የአዲስ ኪዳን 5
®
የቅኔ መጸሀፍት (5)
- የብሉይ ኪዳን 5
- የአዲስ ኪዳን
®
የትንቢት መጸሀፍት (18)
- የብሉይ ኪዳን 17
- የአዲስ ኪዳን 1
®
መልእክቶች (21)
- የብሉይ ኪዳን
- የአዲስ ኪዳን 21
በድምሩ 66 መጸሀፍት ናቸው፡፡
II.
በመጸሀፍ ቅዱስ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
ክርስቲያኖች መጸሀፍ ቅዱስ እ/ር በመንፈሱ
ሰዎችን በመምራት ሀሳቡን ያስተላለፈበት የእ/ር ቃል ነው ብለው ያምናሉ፡፡ እስከ 19 ክ/ዘመንም ይህን አመለካከት የሚቃወም ሀሳብ
ባለመኖሩ እ.ር ቃልነቱ እምብዛም አከራካሪ ያልሆነ ዶክትሪን ነበር፡፡ ነገር ግን በ19 ክ/ዘ በመጸሀፍ ቅዱስ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች
ብቅብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎችም ክርስቲያኖች ምላሽ ለመስጠት የመጽሀፍ ቅዱስ የ እ/ር
ቃልነትን አስመልክቶ የራሳቸውን ዶክትሪን አዘጋጁ፡፡
በመቀጠል
መጸሀፍ ቅዱስን አስመልክተው የሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንሞክራለን
ጥያቄ ፩፡ መጸሀፍቱ በሰው ስለተጻፈ ስህተት አይገኝባቸውም
ቀደም ሲል ለመጥቀስ እንደሞከርኩት መ/ቅዱስ በ1400 አመታት
40 በሚደርሱ ጸሀፍት ነው የተጻፈው፡፡ ስለዚህ መ/ቅዱስ የተጻፈው በሰዎች እጅ ነው፡፡ መ/ቅዱስ በሰዎች እጅ ብቻ ስለተጻፈ ስህተት
ይፈጠራል ወይ? ስህተት ከተፈጠረስ ምን አይነት ስህተት?
በክርስትና መ/ቅዱስ የሰው ልጅ ስለ እ/ር በአጠቃላይ መገለጥ
ያልደረሰበትን መረዳት ይችል ዘንድ እ/ር እራሱን በልዩ ሁኔታ የገለጠበት መንገድ ነው፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው?
እ/ር አምላክ ሐሳቡን ለሰው ለጆች ማሳወቅ ስለፈለገ ለመንፈሱ
ሰዎችን እየነዳ እነዚህ መፅሐፍት እንደፃፉ አደረገ፡፡ ስለዚህ መፅሐፍት ይፃፍ በነበረበት ጊዜ መሪው የአግዚአብሔር መንፈስ ነበር፡፡
ይህ ማለት ግን የሰዎች ድርሻ አለነበረም ማለት አይደለም፡፡ ሰዎች የራሳቸውን ድርሻ ፅሑፎቹን ለማዘጋጀት በመትጋት ተወጠተዋል፡፡
ስለዚህ መፅሐፍቱ የተፃፉት ሉዓላዊ እና ፍፁም ትክክለ በሆነው መንፈስ መሪነት በመሆኑ ምንም አይነት ስህተት አይገኝባቸውም፡፡ ነገር
ግን እንደ ስህተት ሊቆጠሩ የሚችሉ አንድ አንደ ነጥቦች አሉ፡፡ እነሱን በሚቀጥለው ጥያቄ ውስጥ እንመለከታቸዋለን፡፡
ጥያቄ ፪፡ ስህተት ከገባ ትክክለኛውን እንዴት ከስህተት ልንለየው እንችላለን?
በመጀመሪያው ጥያቄ ማብራሪያ ላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት መ/ቅዱስ
ፍፁምና ስሕተት አለ የሚሉ ሰዎች ስሕተት የሚሉትን አቅርቡ ቢባሉም ከፀሐፊዎቹ የመነጨ ስሕተት ሊያቀርቡ አይችሉም፡፡ ነገር ግን
ሙስሊሞችና ሞርሞኖች መ/ቅዱስ በየጊዜው እየተገለበጠ የመጣ በመሆኑ ተዛብቷል
ብለው ይናገራው ይህም ቢሆን ፍፁም ስሕተት ነው፡፡
ለምሳሌ ፡- አዲስ ኪዳንን ብንመለከት ከጥንቱ ታሪክ በብዛት
የተገለበጠ ወይም ኮፒ የተደረገ የመፅሐፍ አይነት ነው፡፡ አሁን በእጃችን ያለውን እና የጥንቱን ግልባጭ ብናነፃፅር 98.33% ትክክለኛና
ምንም አይነት ልዩነት የሌለው ነው፡፡ 150000 ከሚደርሱ ልዩነት ካመጡ ቃላት ውስጥ 400 የሚሆኑት ብቻ የምንባቡ ትርጉም ላይ
በተወሰነ መልኩ ተፅዕኖ ያላቸው ሲሆን ነገር ግን አንድመ የቃል ልዩነት በእምነት ጉዳይ ላይ ያለውን የምንባቡ መለዕክት ላይ ምንመ
አየነት ተፅዕኖ ማምጣት የሚችል አይደለም፡፡ (Companion to the greek testamentand English
version, p.77 ) በመፅሀፍ ቅዱሳችን አንድ ወይም ሁለት አረፍተ ነገሮች ላይ ተፅእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ የመጸሀፍ ክፍል ልዩነቶች
ዮሀ 17፡38-ዮሀ8፡11 እና ማር 16፡9-20 ብቻ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በጥነት ግላባጮች እና ቅጂዎች መካከል በቃልም ሆነ
በአንቀፅ ልዩነት አለ የቃለ ልዩነት ካለ የሐሳብ ልዩነት አለ ማለት ግን አይደለም ቢኖርም እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ ከላይ የጠቀስናቸውን
ጥቅሶች የዚህ ማሳያ ሲሆኑ በዮሐንስ እና በማርቆስ የተፃፉ አይመስሉም፡፡ ይሁን እንጂ ጥያቄው ሌላ ሰው ፃፋቸው ወይስ ቆይተው ተጨመሩ
የሚል እንጂ ስሕተት የመሆን እና ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ (reasonable faith chiristian truth and
apologetics, p.194) ስለዚህም ይህን ለመመልከት መፀሀፍ ቅዱስ ፍፁም ከስህተት የፀዳ በመሆኑ ማንም ሰው ያለ ስጋት ሊያነበው
ይችላል፡፡
ጥያቄ ፫፡ ሰዎች ሲፅፉ በዘመናቸው እውቀት ተወሰኑ ወይስ አልተወሰኑም?
የእ/ር ሰው ፍፁም ለበጐ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእ/ር
መንፈስ ያለበት መፅሀፍ ለትምህርትግና ለተግሣፅ ልብንም ለማቅናትና በፅድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል፡፡ 2ጢሞ 3፡16-17
ሐዋሪያው ጵውሎስ በመልክቱ የመፅሐፍ ቅዱስን ዋና ዋና ጠቀሜታዎችን ሲዘረዝር
1ኛ. ለትምህርት
2ኛ. ለተግሣፅ
3ኛ. ለብን ለማቅናት
4ኛ. በፅድቅ ላለው ምክር ብሎ የዘረዘረዋል
እነኚህን 4 ነጥብች ስንመለከት በዘመናት ውስጥ የሚወሰኑ እውቀቶች
ናቸው ወይ? የሚለውን መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ሕይወትን በፅድቅ መንገድ የመምራት እውቀት በምንም አይነት መልኩ በዘመን እውቀት የሚገደብ
አይደለም፡፡
ነገር ግዘን መ/ቅዱስ ለተለያዩ ማህበረሰቦችና ባበዓሎት አንዲሁም
ቋንቋዎች የተፃፈ መፅሐፍትንም ጭምር ያካተተ መፅሐፍ ነው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ የመልዕክቱ ተቀባዮችን -------------
መልዕክቶች አሉ ማለትም በቋንቋ በባዓል እንዲሁም በእውቀት በመጀመሪያው አድማጭ ማህበረሰብ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡ ከላይ ከዘረዘርናቸው
ነጥብች አንፃር ስንመለከት ግን የመልዕክቶቹ ዋና ሐሳብ ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ሀሳብ ነው፡፡ ስለዚህ መፅሐፍቱ በዘመኑ እውቀት
የተወሰኑት በመጀመሪያዎቹ አድማጮች ባላቸው መለዕክት እንጂ በዘላለማዊው ወይንም በዋናው መንፈስ ያለበት መፅሐፍ አላማ ምንም የእውቀት
ውስንነት የለም፡፡
ጥያቄ ፬. ስለ መ/ቅዱስ ብዙ አተረጓጐም እንዳለ የታወቀ ነው የትኛው ትክክለኛ እንደሆነ በምን
ልናውቅ እንችላለን?
በአሁኑ ሰዓት በአለማችን ላይ መ/ቅዱስ ከ2000 በሚበለጡ ቋንቋዎች
ተተርጉሟል፡፡ ይህ ማለትም ከ90 በ 100 በላይ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ ተዳርሷል ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም 1000 የሚጠጉ
አደደስ ስራዎች በመከናዎን ላይ ናቸው፡፡
ሌላው ጉዳይ መ/ቅዱስ በአንድ ቋንቋ ከተተሮገመም በኃላ አሁንም
ሌሎች ትርጉሞች መቀጠላቸው ነው ለዚህም በቂ የሆነ ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት መ/ቅድስ ከተፃፈበት ዋና ቋንቋ ጋር
ይያያዛል፡፡ በሂደት የተለያዩ ጥንታዉ ቅጂዎች መገኘታቸው እና የዘርፉ ሙሑራን ጥንታዊ የሆኑትን ቋንቋዎች በበለጠ መረዳት መቻላቸው
በጥንት በነበሩ ትርጉሞች ላይ የነበሩ ቭዥታዎችን ለማጣራት አስችሉቸዋል፡፡
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከቋንቋ አድማጭና ለውጥ ጋር የተያያዘ
ነው፡፡ የአንድ ቋንቋ አጠቃቀምና አተረጓጐም በዘመንና በትውልድ ውስጥ ይቀያየራል በዚህ መሰረት አዳዲስ ትርጉሞች ያስፈልጋሉ፡፡
በዘመናችንም እጅግ የበዙ የመ/ቅዱስ ትርጉሞች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ የትርጉሞቹ መብዛትም አንዳንድ ሰዎች የትኛው ትርጉም ነው
ትክክል የሚል ጥያቄ እንዲነሳ ያስገድዳቸዋል፡፡ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ከመሞከራችን በፊት ዋና ዋና የሆኑትን የአተረጓጐም ስልቶች
እንመልከት፡፡
1ኛ. Formal Equivalent ፡- ይህ የትርጉም ዘይቤ
“ቃል በቃል” በቀጥታ ለመተርጎም መሞከር ሲሆን፡፡ ዋናው ቋንቋ ቃላትን ትክክለኛ አቻ ቃል በመፈለግ መተርጎም ነው፡፡ ይህ የአተረጓጐም
ዘይቤ ጠንካራ ጎኖች ቢኖሩትም አቻ ቃላት ላይ ስለሚያተኩር በቋንቋዎች መካከል ያሉ ልይነቶች ተፅዕኖ ያሳድርበታል፡፡
2ኛ. Dynamic Equivalent:- ይህ የአተረጓጐም ዘይቤ
ሐሳብን በሐሳብ ለመተርጐም ይሞክራል ይህ አተረጓጐም የምንባቡን አምድ በመጠቀም በመጠበቅ ለይ ያተኩራል፡፡ ከቅላት ይልቅ ይህም
የትርጉም ጠንካራ ጎኖች ያሉት ቢሆንም በጠቅላላ ጥናት ግን አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
3ኛ. Optimal Equivalent:- የዝህ አተረጓጐም ቀዳሚ
ግብ የተቀባይ ቋንቋ እስከፈቀደው (እስከቻለው) ድረስ ከዋናው ቋንቋ ሀሣቡን በሙሉ መተርጐም ነው፡፡
- ይህ የአተረጓጐም ዘይቤ ከ Formal Equivalent ጋር
ተመሣሣይ በሙስሊም የቋንቋዎች ያለውን ተፅዕኖም ጐን ከዓመት ውስጥ ያስገባል፡፡ በአካሄዱ Formal Equivalent በቀዳሚነት
ሳይሆን ሲቀር ግን Dynemic Equivalent ን አቻችሎ የሚያስኬድ ነው፡፡
4ኛ. Parephrese:- ይህ የአተረጓጐም ዘይቤ መፅሀፉና
የመልዕክቱን ሀሣብ ሣይለቅ ቀለል ባለ ቋንቋ በመተርጐም በቀላሉ መረዳት ማስቻል ላይ የሚያተኩር ነው፡፡
·
መፅሐፍ
ቅዱስን ምንም ከሆኑት ቋንቋዎች (አረማይክ፣ ዕብራይስጥና ግሪክ) ወደ ተቀባይ ቋንቋዎች ለምሣሌ አማርኛ የመተርጐም ስራ ከቋንቋው
ተፈጥሮ እና ተግባቦት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ያካትታል፡፡ ዋና ግብ ግን የቋንቋውን ውበት ያጠበቀ ስነ መሎኮታዊ እሳቤዎችን የሚያከብር እና በዋናነት መጽሀፉን
መልእክት የጠበቀ አማርኛ መ/ቅዱስ ለአንባቢያን ማዳረስ ነው፡፡ ስለዚህ
በመፅ በመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች መካከል ያለው መጠነኛ ለዩነት የሚመነጨው ካተተረጐሙበት የአተረጓጐም ዘይቤ እንደመሆኑ መጠን በዚህ
ረገድ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን ለማራቅ የማጥኛ መፅሀፍትን መጠቀም ጠቀሜታ አለው፡፡
ጥያቄ
፭፡ የመጸሀፍ ቅዱስን ትክክለኛ ዝርዝር /ቀኖና; እንዴት ማወቅ እንችላለን
በመጀመሪያ
ቀኖና የሚለውን ቃል መተርጎም አለብን፡፡ ቀኖና /canon/ ከግሪክ ‘kanon‘ የመጣ ሲሆን ትርጉሙም መለኪያ ወይም መመሪያ ማለት
ነው፡፡ ስለዚህ የመፀሀፍ ቅዱስ ቀኖና ማለት በመጸሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚካተቱ መጸሀፍትን በመለኪያው መሰረት መዘርዘር ማለት ነው፡፡
I. የአይሁድ ቀኖና
የእብራውያን መጽሀፍት ቅዱድስ መጸሀፍት ለመባል በ3 ደረጃዎች
ተሰብስበዋል፡፡ እነዚህ 3 ቅደም ተከተሎች ከ3ቱ የመ/ቅዱስ አካላት ጋር ተነፃጻ ሪነት አላቸው፡፡(የህግ፣የትንቢት እና የቅኔ)፡፡
i. የህግ መጸሀፍት/Torah/ የመጽሀፉ አካ የሆኑት በባቢሎን ምርኮ(538ዓዓ)
እና በሰማሪያ ከይሁዳ መገንጠል መካከል በግምት በ300ዓዓ ሲሆን ሰማሪያ ቶራን ብቻ ትቀበል ነበር፡፡
ii. ሁለተኛ ደረጃ የትንቢት መጽሀፍት /Nebiim/ ናቸው፡፡የእነዚህ
መጽሀፍት ቀኖና የተጠናቀቀው ከ200ዓዓ በፊት በነብዩ ሚልኪስ የትንቢት መተሀፍ ነው፡፡
iii. ሚልኪያስ የመጨረሻው ነብይ ተብሎ ቢታሰብም ሌሎች መፅሀፍትም
ግን መጻፋቸውን ቀጥለው ለአምልኮ እና ለጥናት ያገለግሉ ነበር፡፡መጸሀፈ ሲራክ በተጻፈም ጊዚ(70ዓም) የአይሁድ ቀኖና አልተዘጋም
ነበር፡፡በ1ኛው ክ/ዘ መጠናቀቂያ ግን በፓለስታይን ይኖሩ የነበሩ የአይሁድ ምሁራን ሶስተኛውን ደረጃ ማለትም የቅኔ መፅኃፍጽን
/Ketubim/ በመዘርዘር ቀኖናውን ዘጉት፡፡
v በአይሁድ ቀኖና ብዙዎቹ ውሳኔዎች ተላልፈው በስራ ላይ የነበሩ
ሲሆን የህግ መጽሃፈት የትንቢትና የቅኔ መጽሀፍት በአብዛኛዎቹ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነበር፡፡ ውዝግብ ያስነሱትም በጣም ጥቂት መጽሀፍት
ነበሩ፡፡ ለምሳሌ የመክብብ መጽሀፍ እና መሐልየ መሐልየ ዘሠለሞን አወዛጋቢ ነበሩ፡፡
v በቀኖናው ውስጥ ከተካተቱት መጻህፍት በኋላ የአይሁዳውያን ታሪክ
በተለያዩ መፃህፍቶች ለምሳሌ መቃባውያንን በመሳሰሉት የተመዘገቡ ቢሆንም እንደ እ/ር ቃል ተቆጥረው ግን ከቀደሙት መጸሀፍት ጋር
አልተቀላቀሉም፡፡ ይህም የሆነበት ምክያኒያት ከነብዩ ሚልኪያስ በኋላ የተነሳ ነብይ ባለመኖሩ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሃንስ እስኪነሳ ድረስ፡፡
v በአዲስ ኪዳንም ቢሆን በአይሁድ የሀይማኖት መሪዎች እና በኢየሱስ
መሀል የብሉይ ኪዳን ቀኖናን አስመልክቶ ምንም አይነት ልዩነት የለም፡፡ ኢየሱስ እና የአዲስ ኪዳን ጸሀፊዎች 300 ያህል ጊዜ ከብሉይ
ኪዳን እንደ ባለመለኮታዊ ስልጣን የተቀሱ ሲሆን አንድም ጊዜ ግን ከአፖክሪፋም ሆነ ሌሎች መጽሀፍት መለኮታዊ ስልጣን እንዳላቸው
አድርገው አልጠቀሱም፡፡ ስለዚህ ብሉይ ኪዳንን በተመለከተ 39 የአይሁድ ቀኖና በጣም ትክክል እና አግባብነት ያለው ነው፡፡
Ø የአፖክሪፋ
መጽሀፍት/ The Apocrypha/
አፖክሪፋ የግሪክ ቃል ሲሆን ስውር ወይም የተደበቁ ነገሮች ማለት
ነው፡፡ 14 ወይም 15 የሚጠጉ ከ3 ክ/ዘ ዓዓ እስከ 1ክ/ዘ ዓም የተከናወኑ ዋናዋና የአይሁድ ባህልና ታሪክ የያዙ ተጨማሪ መተሀፍት
ናቸው፡፡ አይሁድ እነዚህን መጽሀፍት በፍጹም እንደ መጸሀፍ ቅዱስ አይቀበሏውም ነበር፡፡ነገርግን በቀደመችው የቤ/ክ ታሪክ እነዚህ
መጽሀፍት ጉዳይ እጅግ አከራካሪ ነበር፡፡ የቀደሙትም ክርስቲያን አባቶች እነዚህን መጽሀፍት በመ/ቅዱስ ዝርዝር ውስጥ አያካትቷቸውም
ነበር፡፡
ቄስ ሚሊቶ የተባለው የሳርዴስ ቄስ በ170ዓም የዘረዘራቸው
66ቱን መጽሀፍት ብቻ ነበር፡፡ሌላው በ404 ዓም ጄሮም የተባለው ተርጓሚ የላቲን ትርጉሙን ባጠናቀቀበት ወቅት የአፖክሪፋ መትሃፍትን
ያካተታቸው ቢሆንም በቀኖና ውስጥ የሚካተቱ ሳይሆን ለእምነት የሚጠቅሙ መጽሀፍት ናቸው ብሎ ነበር፡፡ እነዚህን መጽሀፍት አስመልክቶ
ግን ትልቁ ውሳኔ የተላለፈው በ1546ዓም በትሬንት ጉባኤ ነበር፡፡ የማርቲን ሉተርን እንቅስቃሴ እና የፕሮቴስታንት መስፋፋትን ለመቃወም
በተደረገው ጉባኤ የሮማን ካቶሊክ ቤ/ክርስቲያን ከ3ቱ መጽሀፍት ውጪ ያሉን በሙሉ በቀኖናዋ ውስጥ አካታቸው ነበር፡፡
v እነዚህን መጽሀፍት ላለመቀበል 7 ዋናዋና ምክኒያቶች አሉ፡-
1.
አይሁዳውያን
አልተቀበሏቸውም
2.
የመጸሀፍቱ
ተቀባይነት በጣም ውስንና ጊዜያዊ ስለነበሩ
3.
የታወቀ
የበ/ክ ጉባኤ/አብይ ጉባኤ/ መጽሀፍቱን አልተቀበለም
4.
ብዙዎቹ
መጽሀፍት ስህተት ይገኝባቸዋል
5.
ከመ/ቅዱስ
ሃሰብ የሚቃረኑ ሀሳቦች አሉባቸው(ለምሳሌ ለሙታን የሚደረግ ጸሎት)
6.
መጽሀፍቱን
የተቀበሉ በ/ክኖች ይህንን ያደረጉት ቀኖናው ከተጠናቀቀ ከብዙ አመታት በኋላ ነው፡፡
7.
መጽሀፍቱ
በአዲስ ኪዳን እንደ መለኮታዊ ባለስልጣን አልተጠቀሱም
II. የክርስቲያን ቀኖና/የአዲስ ኪዳን ቀኖና/
ቀደም ሲል በአይሁድ ቀኖና ስር የብሉይ ኪዳን ቀኖናን ስለተመለከትን
ቀጥታ ወደ አዲስ ኪዳን ቀኖና እንሸጋገራለን፡፡
·
አትናቲዎስ
የተባለው የአሌክሳንድሪያ ቄስ 27ቱን የአዲስ ኪዳን መጽሀፍት በ367 ዓ.ም ዝርዝር አውጥቶ ነበር፡፤ በተጨማሪም አትናቲዎስ ቀኖና
የሚለውን ቃል የተጠቀመ የመጀመሪያው የቤ/ክ አባት ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪ የካርቴጅ ጉባኤ (393ዓም) እና የሂፖ ጉባኤ(397ዓም)
የመጨረሻው የአዲስ ኪዳን ዝርዝር ላይ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
·
አራት
ዋና ዋና ምክኒያቶች ቀኖነው እንዲዘጋ ምክኒያ ቶች ሆነዋል፡፡
1.
የሀሰት
መልእክቶች በክርስቲያኑ መሀል መዘዋወር መጀመራቸው
2.
የተሳሳቱ
መልእክቶች በሀዋሪያት ስም መዘዋወር መጀመራቸው
3.
ሚሽነሮች
ወደአዳዲስ ቦታዎች ሲሄዱ የትኞቹን መጽሀፍት መጠቀም እንዳለባቸው ለማሳወቅ
4.
በ303
ዓም በወጣው ክርስቲያናዊ ጽኁፎችን የማጥፋት ትእዛዝ ክርስቲያኖች
የትኞቹ መጽሀፍት መጠበቅ እንደሚገባቸው ለማሳወቅና ለየትኞቹስ ዋጋ መክፈል እንደሚገባ ለማሳወቅ፡፡
·
የቀደመቸው
ቤ/ክ መጽሀፍትን በቀኖና ለማካተት መስፈርቶች ነበሯት
ü በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ስለመጻፉ ፍንጭ ስለመኖሩ
ü መጸሀፉ የተጻፈው በሐዋሪያ ወይም ለሐዋሪያ ቅርብ በሆነ ሰው
ስለመሆኑ
ü መጸሀፉ የተጻፈው ሐዋሪያው በህይወት በነበረበት ወቅት ስለመሆኑ
ü መጽሀፉ በቤ/ክ ተቀባይነት እና ለአምልኮ ስርአት አገልግሎት
ላይ ስለመዋሉ
ü ከሌሎች የመ/ቅዱስ መጸሀፍት ጋር ስለ መስማማቱ
·
ስለዚህ
የጥንት አባቶችን እና የቤ/ክ መሪዎች ያወጧቸውን ዝርዝሮች በመመልከት እስትንፋሰ እ/ር ያለባቸው መጽሀፍት ዝርዝር 66ቱ ናቸው፡፡
ጥያቄ ፮. እ/ር የመፅሐፍ ቅዱስ ፀሐዎዎችን እንዴት መራቸው? በእ/ርና በአነርሱ መካከል ምን አይነት ግንኙት ነበር? ፀሀፊዎች ሲፅፉ
ቀኖናዊ መፀሐፍ መፃፋቸዉን ዓወቁ ወይስ አላወቁም?
Ø
በመፅሐፍ ቅዱስ ከ1400 ዓመት በላይ በፈጀ ጊዜ ከ40 በሚበለጡ ፀሀፍት ተፃፈ፡፡
40ው ፀሀፍት በተለያየ ጊዜና ቦታ በፅፉም የሚፅአት መልዕክት ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የመልዕክቱ ባለቤት እ/ር
በመሆኑ በው ሀሣቡን አንዲፅፍ ስለተጠቀመበት ነው፡፡
Ø
የብሉይም
ሆነ የአዲስ ኪዳን ፀሐፊዎች ከእ/ር ጋር የተለየ ቅርርብ የነበራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ሙሴ፣ እያሱ፣ እዝራ ፣ ዳዊት ፣ ኢሳያስ፣
ማቲዮስ፣ ጳውሎስ፣ ዮሐንስ…. የመሳሰሉት ሁሉም አምላካቸውን የሚፈሩና የሚያከብሩ እ/ር የሚጠቀመባቸው ሰዎች ነበሩ፡፡
Ø
ቀኖና
መፃፍ አለመፃፋቸውን ስለማወቃቸው ለመናገር ትንሽ አስቸግሪ ነው፤ ቀኖና የሚለው ሐሳብ የመጣውም መፅሐፍቱ ከተፃፉ ብዙ አመታት በኃላ
ከመሆኑ አንፃር፡፡ ነገር ግን በአንድ ነገር አርግጠኛ መሆን አንችላለን፤ የሚፅፉት የእ/ር ሐሳብ ላይ መሆኑን በማወቃቸው ጉዳይ
ላይ፡፡ በተለየ ሁኔታ ግን ጳውሎስ በቆላ4፡16 እና 1ተሰ5፡26 መለዕክቱ በጉባኤ እና በሌሎች ቤተክርስቲያኖች እንደሚነበቡ ማወቁን
የሚጠቁሙ ጠቅሶች አሉ፡፡
© እኛ እንደ ክርስቲያን ግን በአንድ ነገር እናምናለን መ/ቅዱሳችንመንጩ እ/ር ስለመሆኑ፡፡ መፅሐፉንም የሰጠን አርሱ እንድናውቀው ነው፡፡ ስለዚህ በአያንደንዱ መ/ቅዱስ ተኮር እንቅስቃሴ ውስጥ የእ/ር
መለኮታዊ ተፅዕኖ ነበር/ አለ፡፡ ከዚህ የተነሳ ቃሉ አስካሁን የሰራለ በሰው ሕይወትም ለውጥ ያመጣል፡፡
No comments:
Post a Comment