ስለ ኢየሱስ
በመፅሀፍ ቅዱሳችን በሐዋሪያት ስራ ምዕራፍ
11 ደቀመዛሙርት ለመጀመሪያ ጊዜ በአንፆኪያ ክርስቲያን ተብለው ስለመጠራታቸው ተፅፎ እናነባለን፡፡ ክርስቲያን የሚለው ቃል ከሐዋሪያት
ስራ ምዕራፍ 11 በፊት በተደጋጋሚ ከ ቤተ-ክርስቲያን ጋር ተያይዞ ቢጠቀስም የሁሉም መነሻ ግን ለአማኞች በአንፆኪያ የተሰጠው ክርስቲያን
የሚል ስያሚ ሆኖ አናገኝዋለን፡፡ የቃሉን ፍቺ ስንመለከት ደግሞ የክርስቶስ ተከታዮች ወይም የክርስቶስ ባሪያዎች የሚል ትርጉም አለው፡፡
ከዚያም ጊዜ አንስቶ ቃሉ በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ መጠሪያ ሆኗል፡፡ ቤተ-ክርስቲያንም ከዚህ ህብረት የተገኝች ሲሆን በመጀመሪያዎቹ
የታሪኳ ክፍለ ዘመናት ከፍተኛ በሆነ ስደትና መከራ ውስጥ አልፋለች፡፡
ቤተክርስቲያን ነፃነቷን ከተቀናጀችባቸው አመታት
በኋላ ያሉት ጊዜያት ደግሞ በክርስቲያናዊ ፍልስፍና፣ ክርክርና ጉባኤዎች የታጀበ ነበር፡፡ የክርክሮቹም ሆነ የጉባኤዎቹ ሙሉ ትኩረትና
ሃሳብ ማእከሉን ያደረገው በክርስቶስ ማንነት ጉዳይ ላይ ነው፡፡ በየጉባኤዎቹም የቤተ-ክርስቲያን አባቶች ክርክሮችን ካደረጉ በኋላ
ውሳኔዎችንም ያስተላልፉ ነበር፡፡ በክርሰትቶስ ላይ የሚነሱት ጥያቄዎች ግን ከመቆም ይልቅ በተለያዩ መልኮች ቀጥለዋል፡፡ ቤተ-ክርስቲያንንም
ለሁለት እስኪከፍል ድረስ የክርስቶስ ማንነት ጉዳይ እጅግ ተፅእኖ ፈጣሪ ጥያቄ ነበር፡፡ እስካሁንም ድረስ በክርስቶስ ማንነት ላይ
እጅግ በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ሁሉም በየፊናው ለነዚህ ጥያቄዎች የየራሱን ምላሽም ለመስጠት ይሞክራል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶች የክርስትና መሰረትና ማእከል
እነደመሆኑ መጠንና ከመለኮት ጋር መያያዙ በማንነቱ ላይ ብዙ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ ምናልባት ያን ያህል አስገራሚ ነገር ላይሆን ይችላል፡፡
ነገር ግን ለመሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽን መፈለግ በዚህም መረዳት እንደ ክርስቲያን ክርስቶስን መከተል በጣም አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡
በዚህ ዘመን ቤ/ክርስቲያንም በክርስቶስ ላይ
ለሚነሱ ጥያቄዎች የሚሰጡ ምላሾች እንደጥያቄዎቹ ሁሉ ብዙ ናቸው፡፡ የአንዱ ምላሽ ለሌላው ኑፋቄ ሆኖም የሚገኝበት አጋጣሚም ብዙ
ነው፡፡ በአንድ ህብረት ውስጥ የሚያገለግሉና ህብረት የሚያደርጉ አማኞች አመለካከትም እጅግ በጣም የተለያየ ሆኖ የሚገኝበት አጋጣሚም
ቀላል አይደልም፡፡ በአጭሩ ስለ አንዱ ስለ ኢየሱስ እጅግ ብዙ አመለካከቶችና እመነቶች አሉ፡፡
ከዛሬ 20 እና 30 አመት በፊት ከነበረው ሁኔታ
ጋር ስናነጻጽረው አሁን ቤተክርስቲያ ያለችበት ሁኔታ የተለየ መሆኑን መረዳት አያዳግትም፡፡ በእርግጥ በተለይ ከወንጌላውያን አማኞች
አንፃር ስንመለከተው የምእመናን ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው በብዙ እጥፍ ጨምሯል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠረው አማኝም ቀላል የማይባለውን
የሃገሪቱን ህዝብ ቁጥር ድርሻ ይዟል፡፡ ይህ ቁጥርም በየጊዜው በመጨመር ላይ መሆኑ የማይታበል ሃቅ ነው፡፡ ይህ በእውነቱ በጥቅሉ
ስናየው በጣም ትልቅ በረከት ነው፡፡ ቢያንስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ ጌታ ሰምተው ተቀብለዋል ማለት ነው፡፡ ይህ በራሱ ግን
በቂ ነው ማለት አይደለም ምክኒያቱም ኢቲዮጲያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጲያ ውጪ ብዙ ያልተሰሩ የቤት ስራዎች አሉ፡፡ ገና ሊደረስባቸው
የሚገቡ ቦታዎች አሉ፡፡ ቤ/ክርስቲያን ደግሞ ከዚህ የሚበልጥ ሌላ አጀንዳ የላትም፡፡ ይህም አጀንዳ ታላቁ ተልእኮ ወንጌልን ለፍጥረት
ሁሉ ማድረስ ነው፡፡
ይህን በመፈፀም ረገድ ግን ቤ/ክርስቲያን አሁን
ያለችበት ጊዜ ከዚህ በፊት ካለው ጋር ሲነጻጸር መለወጡ በወንጌል መስፋፋት ረገድ ብቻ ሳይሆን በህብረተሰቡ ውስጥ እየመጣ ያለው
የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥም ጭምር ነው፡፡ ይህ የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ወንጌል የሚነገረው ሰው በእምነት መቀበልን
ብቻ ሳይሆን በአመክኒዮ የሚሞግት መሆኑ ጭምር ነው፡፡ በአመክኒዮ መቀበልም ሆነ አለመቀበል በፊትም የነበረ ቢሆንም አሁን የሚንፀባረቀው
ግን ከኢ-አማንያን የሚነሱት ጥያቄዎች እንኳን ከመፅሃፍ ቅዱስና ከክርስትና አመለካከት የሚመነጩ መሆናቸው ነው፡፡ ይህን ወቅታዊ
ተግዳሮት ያለፈ የወንጌል ስርጭት እንዲኖር ደግሞ ክርስቲያኑ ማህበረሰብ በትክክለኛውና መፅሃፍ ቅዱሳዊ በሆነው መረዳት ላይ መመስረትና
ለሚጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ምክኒያቱም ወንጌልን ማሰራጨት በቤ/ክርስቲያን ውስጥ ላሉ የተወሰኑ ሰዎች የተሰጠ
ሃላፊነት ሳይሆን ለሁሉም አማኝ የተሰጠ ሊፈፀም የሚገባው ታላቅ ተልእኮ በመሆኑ ነው፡፡
ቤ/ክርስቲያን ወንጌልን ከማሰራጨት ጎን ለጎንም
መንጋውን የመጠበቅና የመመገብ ሃላፊነትም አለባት፡፡ በዚህ ዘመን ሌላው የቤተክርስቲያን ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ የምናገኝው ይህ ነው፡፡
አማኙ ማህረሰብን የቤ/ክርስቲያን አባል ከማድረግ በዘለለ እውነተኛ ደቀመዝሙር እንዲሆን ከማድረግ አንፃር መሰረታዊ ችግሮች ይታያሉ፡፡
ይህም አማኙ ለስህተት ትምህርቶች የተጋለጠና በየጊዜው ለሚመጡ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ላልሆኑ ልምምዶች አጋልጦታል፡፡ ዘመናችን ደግሞ ከእውነተኛው
እምነትና ከትክክለኛው አኗኗር ገለል በሚያደርጉ አልባሌ ትምህርቶች የተሞላ ነው፡፡ በትክክለኛ የክርስቶስ መረዳት ላይ የተመሰረተች
ቤ/ክርስቲያንና ምእመን ግን ይህን ሁሉ ችግር ለማለፍ አይቸገርም ስለዚህም ትክከለኛ የሆነው የመፅሃፍ ቅዱስ እውቀት በክርስቶስ
ላይ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
ኢየሱስ የሚለውን ስም መፅሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተፅፎ የምናገኝውበማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ
1 ቁጥር 1 ነው ይኸውም የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መፅሃፍ የመጀመሪያው ምእራፍና የመጀመሪያውቁጥር መሆኑ ነው፡፡ ታዲያ ኢየሱስ
ክርስቶስ ከዚያ በፊት ነበርን? ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት
ግን ስለ ኢየሱስ መመለስ ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ አለ፤ ኢየሱስ ማን ነው? ሰው ወይስ አምላክ?
የብሉይ ኪዳን መፅሃፍ መደምደመያ የሆነው ትንቢተ ሚልኪያስ የብሉይ ኪዳን መፅሃፍትን የሚጠቀልለው
የሚጠብቁት ተስፋ ምጣት ተስፋን በመስጥ ብቻ ሳይሆን በነብዩ ኤሊያስ መንፈስ የሚነሳ ነብይ ቀድሞ እንደመመጣ ጭምር ተስፋ በመስጠት
ነው፡፡ ይህ ትንቢታዊ ቃል ፍፃሜውን መያዝ የጀመረው መጥምቁ ዮሃንስ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ
በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ በመጣ ጊዜ ነበር፡፡ መጥምቁ ዮሃንስም ሲጠብቁት
የነበረው ተስፋ ኢየሱስ መሆነን መሰከረ (ማቴ3፤11-12) ሰማያት ተከፍተውም የአምላክ ልጅ ስለመሆኑ ድምፅ ከሰማይ መሰከረ፡፡
ነገር ግን ህዝቡ አልተገነዘበውም ነበር ማን እንደሆነም አላወቁም ነበር፡፡ ለዚህም ነው ኢየሱስ
ስለ ራሱ በማቴ 16 ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ የጠየቀው፡፡ለዚህ ትክከለኛ የሆነው ምላሽ በጥምቀቱ ቀን ከሰማይ ከመጣው ድምፅ ጋር ተመሳሰይ
ነበር፤ ይኽውም አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ የሚል ነበር፡፡ በእውነት አስደናቂ ነው፡፡ መፅሃፍ
ቅዱስ በገልፅ ኢየሱስ እንዴት ከድንግል ማሪያም በመንፈስ እንደተፀነሰም ይነግረናልና፡፡ ስለዚ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ አምላክ የሰው
ልጅ ሰው ነው፡፡ ይህ ማለትም አንዱ አየሱስ ሰው ነው አምላክ ነው ማለት ነው፡፡ በዚህ ከተግባባን መነሻችን ላይ አንስተነው ወደነበረው
ጥያቄ እንመለስ፡፡ ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ በፊት የት ነበር ዌም ምንድ ነበር?
ኢየሱስ አምላክም ሰውም ነው ካልን ሰው ከመሆኑ በፊት በመለኮትነት ይኖር
እንደነበረ ማወቅ ያን ያህል የሚያደናግር ጉዳይ አይሆንም ግን እንዴት?
መምህር በልሁ ደሳለኝ እኔን ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ በተሰኘው
መፅሃፋቸው የሚከተለውን ብለዋል "ከመፅሃፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ኢየሱስ በቤትልሔም ከድንግል ማሪያም ሲወለድ
እያንዳንዱ ሰው በመውለዱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተገኝ የእርሱም መገኝት እንዲሁ አልነበረም፡፡ ስጋ ሆኖ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት
አስቀድሞ ነበረ፤ ነገርግን ኢየሱስ በመባል አይታወቅም ነበር፡፡"
በዚህ መፅሃፍ ላይ ሲያብራሩ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር አምላክ በብዙ ቁጥር ስም ስለመጠራቱ ማለትም
ኤሎሂም በሚል ስም ስለመጠራቱና በአዲስ ኪዳን ብርሃን ጉዳዩን
ከተመለከትነው እግዚአብሔር በረቂቅነቱ አንድም ሶስትም መሆኑን እንረዳለን ይላሉ፡፡ ይህ በብሉይ ኪዳን ከአንድ በላይ ቁጥር የተጠራውና
በአዲስ ኪዳን በሶስትነቱ የተጠቀሰው አምላክ ከሶስቱ አካላት አንዱ ወልድ ቃል ተብሎ ይታወቅ እንደነበረም ያብራራሉ፡፡
የዮሐንስ
ወንጌል 1
|
|
በመጀመሪያው
ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
|
|
|
ይህ
በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
|
|
ዶ/ር ዴቪድ ሀዊኪነግ Christology
The Doctrine of Jesus Christ በተሰኝው መፅኃፋቸው መፅሃፍ ቅዱሳችንን የዮሃንስ
ወንጌል የመጀመሪያው ምእራፍ ላይ ስንገልጥ በኢየሡስ ክርስቶስ ቅድመ መገለጥ 5 ዋና ዋና ቁምነገሮችን እናያለን 1. ከሁሉ ፍጥረት
የበላይነት 2. ሁሉን ነገር የመፍጠር ብቃቱን 3. ሁሉን የመቆጣጠር ብቃቱን 4. በብሉይ ኪዳን ዘመንም ስለመገኝቱ እና 5. ከሁሉ
መላቁን እንመለከታለን ይላሉ፡፡ በእርግጥም እነዚህ አብይ ጉዳዮች ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ስለመሆኑ እና ማንነቱም ከዘለአለም ስለመሆኑ
ያስረዳል፡፡
በዮሐ 1፡1 ላይ የምናገኝው ቁልፍ ቃል ቃል የሚለው ነው፡፡ በግሪኩም ቴዎስ
የሚል ስር አለው፡፡ ቴዎስ የሚለው የግሪክ ቃል በሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ላይ ከ2000 በላይ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ ያህዌ የመለውን
የእግዚአብሔር ስም ጨምሮ በርካታ የብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ስሞችን ተክቷል፡፡ ይህ ማለት ቅድመ አለም ወልድ የእግዚአብሔር ቃል
በመባል ይታወቃል ነገር ግን ከሰው አንደበት እንደሚወጣና ዝርው (የማይጨበጥ የማይዳሰስ) ቃል ሳይሆን በረቂቅ አካልነት ሆኖ ማን
እነጂ ምን የሚባል አይደለም፡፡ ስለዚህም አካል ቃል ልንለው እንችላለን፡፡
ድህረ ስጋ መሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል
ማሪያም ከተወለደ በኋላ ያለውን ጊዜ የሚያመለክት ነው፡፡ ወይም በሌላ አገላለፅ ይህ ዘመን ማለት መለኮት ስጋን ገንዘቡ ያደረገበትን
ጊዜ ያመለክታል፡፡ በዚህ ዘመን ውስጥ ስላለው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት እጅግ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ቀስ በቀስ የተወሰኑትን
ለማየት እንሞክራለን
ሀ. ኢየሱስፍፁምሰው
መለኮት የነበረው ወልድ ከድንግል ማሪያም በመወለዱ
የሠው ስጋን ለብሶ ፍፁም ሰው ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህ ታዲያ ግር የሚል ነገር እንዳለው አይካድምምክንያቱም መለኮትን ፍፁም ሰው
ሆነ ማለት ለመረዳት አዳጋች ስለሚያደርገው ነው ይህን ጉዳይ ወደኋላ በስፋት እንመለከተዋለን አሁን ግን ስለ ፍፁም ሰውነቱ ከመፅሃፍ
ቅዱስ ማስረጃዎችን እንመልከት፡፡
-
ከድንግል መወለዱ፡-ከድንግል መወለዱ ከትንቢት ፍፃሜነት በዘለለ ሌሎች ፋይዳዎችም አሉት እንደ ዋይን ግሩደም የመጀመሪያው
ፋይዳ ድነትበመሰረቱ ከጌታ መምጣት እንዳለበት ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት ድነታችን በእግዚአብሔር መለኮታዊ ስራ የሚከናወን መሆኑን
ያመለክታል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከድንግል በመወለዱ ፍፁም አምላክነትና ፍፁም ሰውነት በአንድ አካል እንዲዋሃዱ አደረገ፡፡ ሶስተኛው
ፋይዳ ደግሞ የክርስቶስ ከድንግል መወለዱ የውርስ ሃጢያት ሳይኖርበት እውነተኛ ሰው እንዲሆን ያስችለዋል፡፡
-
የሰው ባህሪያትን ማንፀባረቁ፡-የክርስቶስ ልደት እና ስደት ከስደት መልስ ከእናቱ ከማርያም ጋር ዮሴፍ ቤት ማደጉ በአይሁድ ልማድ
አገልግሎቱን እድሜው ሰላሳ አመት ሲሞላው መጀመሩና የአገልግሎቱ ይዘት ይህውም በየሙክራቡ ተገኝቶ በማስተማርና የፈውስ አገልግሎት
እንዲሁም ተአምራትን የማድረግ አገልግሎት ሲሆን ፍጹም ሰው በመሆኑ በአገልግሎቱ ተቃውሞ መድረሱና የክርስቶስ መምጣት ሰዎችን ከዘለአለም
ሞት ለመታድግ ስለሆነ ስለሰው ልጆች ካለው መለኮታዊ ፍቅርና አላማው አኩዋያ ነፍሱን እስከ መስቀል ሞት አሳልፎ በመስጠት ተልእኮውን
መወጣቱን በአጭሩ ስንመለከት የሰዋዊ ባህሪዎቹ መገለጫዎች ናቸው በተጨማሪም መራቡ መድከሙ መተኛቱ መነሳቱመቁሰሉ መድማቱ ሁሉ የሰውነቱ
አስረጂዎች ናቸው፡፡
-
የሌሎች ሰዎች ምስክርነት፡- ማቴ 13፡53-58 ኢየሱስን ያውቁ የነበሩ ሰዎች በተለይም የገዛ
ወገኖቹ ማንነቱን እንዴት ያውቁትና ይረዱት እንደነበረ ያሳየናል
ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው
ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ። ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?
|
ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል
የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?
|
እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን
ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
|
ስለዚህ ከጎረቤቶቹና የገዛ ከተማው ሰዎች በላይ ስለፍፁም ሰውነቱ አስረጂ ማግኝት አይቻልም፡፡
ከላይ በስፋት ለማየት እንደሞከርነው
ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው ነበር ካልን የሰው ባህሪና ፀባይ ከነበረው ኢየሱስ ሃጢያትን ሊሰራ ይችል ነበርን? ሃጢያታዊ ስጋ ነበረውን? ይህ ባህሪስ ካልነበረው ሰው
ነበር ለማለት ይቻላልን?ካልሆነስ እንዴት የሐጢያተኛው ሰው ምትክ ሊሆን ይችላል? የሚሉ ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎችን
የአልቦ ሃጢያት የእምነት አንቀፅ ለብዙ የኑፋቄ ትምህርቶች ምላሽ ይሰጣል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው መፅሃፍ
ቅዱሳዊ እውነቶችን ለመመልከት እንሞክራለን፡፡ በመፅሃፍ ቅዱሳችን ኢየሱስ ሰው ስለመሆኑ ብዙ ምንባቦች ቢኖሩትም በአንድም ቦታ ግን
ሃጢያትን ስለመስራቱ አይነግረንም፡፡ በተቃራኒው እኒዲያውም ከሃጢያት ነፃ ስለመሆኑ ይነግረናል(ዕብ 4፡15-16)፡፡ኢየሱስሰውነበር፤ከድንግልየተወለደ (ማቴ 1፡18፣
20)፡፡ኢየስስከድንግልመወለዱብዙፋይዳዎችያሉትቢሆንምዋነኛውግንእውነተኛየሰውማንነትንያለኀጢአትእንዳይዝማስቻሉነው፡፡ሰዎችሁሉከአዳምየወረሱትየውርስኀጢአትአላቸው፡፡ስለዚህኢየሱስየሰውአባትየለውምማለትከአዳምሊወርሰውየሚችለውኀጢአትበከፊልተቋርጧልማለትነው፡፡ይህኢየሱስከማሪያምለምንኀጢአትንአልወረሰምየሚልንጥያቄያስነሳል፡፡የካቶሊክናየኦርቶዶክስእምነትተከታዮችማሪያምጥንተአብሶ
(ኀጢአት)
አልነበረባትምይላሉ፡፡ሆኖምግንመጽሐፍቅዱስይህንየሚደግፍፍንጭአይሰጠንም፡፡ይልቁንምከመንፈስቅዱስተሳትፎየተነሳኢየሱስያለውርስኀጢአትመወለዱንያስተምራል
(ሉቃ
1፡35)
ሌሎችየመጽሐፍቅዱስክፍሎችምይህንኑያስተምራሉ፡፡ኢየሱስበሰይጣንተፈትኖአልወደቀም
(ሉቃ4፡13)፣ “እኔየአለምብርሃንነኝ” (ዮሐ 8፡12)-
ብርሃን
የሚለው ቃል እውነተኛነትንእናየሞራልንጽሕናንየሚያመላክትነው፡፡ኢየሱስተቃዋሚዎቹን
“ከእናንተበኀጢአትየሚወቅሰኝማንነው”
(ዮሐ
8፡46)
ሲልይጠይቃል፤ጳውሎስኢየሱስን
“ኀጢአትያላወቀ”
በማለትይገልጸዋል
(2ቆሮ
5፡21)፣ጴጥሮስም “ኀጢአትአላደረገም፣ተንኮልምበአፉአልተገኘበትም”
በማለትገልጾታል
(1ጴጥ
2፡22)፡፡የዕብራውያንመልዕክትጸሐፊምእንዲሁ
“በማንኛውምነገርየተፈተነሊቀካሕናትአለን፤ይሁንእንጂምንምኀጢአትአልሰራም”
(ዕብራውያን
4፡15)
በማለትይገልጸዋል፡፡ክርስቶስከማሪያምስጋቢነሳምየነሳውስጋከመንፈስቅዱስየተነሳቅዱስነው፡፡
“የክርስቶስትሥጉትምሥጢርነውናፍጹምአምላክ፥ፍጹምሰውምሆኖውስጣዊስሜቱእንዴትእንደነበረማወቅአንችልም፡፡”
(ቄስማንስል
245) ሌላውከኢየሱስአልቦኀጢያትጋርተያይዞየሚነሳውጥያቄኢየሱስኀጢአትመስራትይችልነበረወይ?
የሚለውነው፤ክርሲያኖችለዚህጥያቄበሚሰጡትምላሽለሁለትይከፈላሉ፡፡የመጀመሪያዎቹኢየሱስኀጢአትመስራትየማይችል
(impeccability) ነበርይላሉ፡፡ኢየሱስየአብንፈቃድሊፈጽምስለመጣከዚህፈቃድውጪበመሆንኀጢአትንሊሰራአይችልም፡፡ከዚህምበተጨማሪየእግዚአብሔርልጅመሆኑኀጢአትንመስራትእንዳይችልያደርገዋልሲሉይሞግታሉ፡፡ሁለተኞቹደግሞኢየሱስኀጢአትንመስራትየሚችልነበር
(peccability) የሚሉትናቸው፡፡ኢየሱስኀጢአትመስራትየማይችልቢሆንኖሮየመፈተኑፋይዳምንድንነው?
ለአማኞችንእንዴትዐርአያሊሆንይችላል?
የሚልየሙግትሃሳብንያቀርባሉ፡፡መጽሐፍቅዱስከላይላነሳነውጥያቄአጥጋቢየሆነንምላሽአይሰጥም፡፡
ለማጠቃለል ከላይበአጭሩለመመልከትእንደሞከርነውምንምእንኳንክርስቶስኀጢአትንመስራትይቻልአይቻልግልጽባይሆንምበዚህምድርሲመላለስክርስቶስኀጢአትንአልሰራም፡፡ቄስማንስልእንዳሉት
“በአዲስኪዳንበክርስቶስንግግርናአኗኗርየኀጢአትምልክትስለመታየቱአንድምፍንጭአይገኝም፡፡”
ለ. ኢየሱስፍፁምአምላክ
የኢየሡስ ክርስቶስ አምላክነት በወንጌል ሲታይ መጀመሪያ ወደ አይምሮአችን የሚመጣው የዮሐንስ ወንጌል መእራፍ አንድ
ነው፡፡ ዮሐ1፡1 ቃልም በመጀመሪያ ነበር ብሎ ይጀምርና ቃልም ስጋ ሆነ ፀጋንና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ ይለናል፡፡ በዚህ
ክፍል ውስጥ የክርስቶስ ኢየሱስ አምላክነትና በአምላክነት ውስጥ አንዱ የሆነውን ፈጣሪነት ያሳየናል፡፡ ይህን ባህሪውን በዮሐ1፡10
እርሱ በአለም ነበር አለምም የተፈጠረው በእርሱነው በማለት ያብራራልናል፡፡ ሌላው ደግሞ የመጥምቁ ዮሐንስ ምስክርነት ነው መጥምቁ
ዮሐንስ "ከእኔ
በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይበልጣል ምክንያቱም ከእኔ በፊት ነበር"በማለት
መስክሯል፡፡
በአጠቃላይ የዮሐንስ ወንጌልን ስናነብ እነዚህን
ሃሳቦቸ እናገኛለን
-
ከዘላለም የአብ ልጅ መሆኑን
-
ከአብ ጋር የሚተካከል መለኮት መሆኑን
-
በምድር ሳለም እንደቀድሞው ያለ ግንኙነት ያለው መሆኑን
ለመንደርደሪያ ያህል የዮሐነስ ወንጌልን ተመለከትን እንጂ ሁሉም የአዲስ ኪዳን ፀሃፊዎች አምላክነቱን በተለያየ መንገድ
ገልፀውታል፡፡
-
ቴዎስ ወይም አምላክ - ሮሜ 9፡5 ፣ ቲቶ 2፡13 ፣ ዕብ 1፡8 ፣ 2ጴጥ 1፡1
-
ጌታ (ኩሪዮስ) - ሉቃ 1፡11 ፣ ማቴ 3፡3 ፣ ማቴ 22፡44 ፣ 1ቆሮ 8፡6
-
እኔ ነኝ - ራእ 22፡13 እነዚህና የመሳሳሉትን በጥቂቱ
ለመጥቀስ ሞከርን እንጂ እጅግ በጣም ብዙ ማስረጃዎችን ማግኝት ይቻላል፡፡
ከላይ ከተመለከትናቸው ባሻገር ግን ኢየሱስ በተግባር አምላክነቱን የሚያረጋግጡ ምንባቦችን ማግኝት ይቻላል፡፡
-
ባህሩንና ማእበሉን ፀጥ ማድረጉ ማቴ 8፡26
-
እንጀራውንና አሳውን ማብዛቱ ማቴ 14፡19
-
ውሃን ወደ ወይን ጠጅ መቀየሩ ዮ ሐ 2፡1-11 የመሳሰሉት ምንባቦችከተፈጥሮ በላይ የሆነ ልእለ ሃይል እንደ ነበረው
አመላካች ናቸው፡፡ ከሁሉ በላይ አሰደናቂ የሆነው የመለኮታዊ ስልጣኑ አስረጂ ግን በማር 2፡5-7 ይገኛል ይኽውም ሃጢያትን ይቅር
የማለት ስልጣን ነው፡፡
ሐ. ኢየሱስፍፁምአምላክፍፁምሰው
ስለ
ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክነትና ፍፁም ሰው መሆን ከመፅሃፍ ቅዱስ ማስረጃዎችን አየን፤ አሁን ትልቁ ጥያቄ የሚሆነው ታዲያ አነዚህ
የተለያዩባህሪያት በአንድ እንዴት መገኝት ተቻላቸው የሚለው ሃሳብ ነው፡፡ ኢየሱስ በአንድ ጊዜ እንዴት ሰውም አምላክም መሆን ተቻለው?
ይህን
ጉዳይ አስመልከቶ ሽመልስ ይፍሩ "የተመለሱና ያልተመለሱ
ጥያቄዎች" በሚል ርእስ ባዘገጁት መፅሃፋቸው ያነጋገሯቸው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን አባት የክርስቶስ
ፍፁም ሰውነትና ፍፁም አምላክነትን ሲያስረዱ ክርስቶስ መለኮትና ሰው
ተዋህዶ ፈጥረውወደ አንድ ማንነትና ባህሪ የመጡበት አንድ አካል ነው፡፡ይህም አካል ሰው የሆነ አምላክ እንደሚባል ያስረዳሉ፡፡
ይህ ማለት ግን ሰውነት ወደ አምላክነት መለወጥን ወይም አምላክነት ወደ ሰውነት መቀየርን አያመለክትም ብለዋል፡፡ ነገር ግን አንዱ
አንዱን በተዋህዶ ፍፁም ገንዘቡ ማድረጉን እንጂ ሁለቱ ባህሪያት በፍፁም እንደማይቀላቀሉ ተናግረዋል፡፡
በእውነቱ
ከላይ የቀረበው አባት ሃሳብ በጣም ጥሩና አሰማኝ ገለፃ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሌላ ደግሞ አከራካሪ ጥያቄ ይነሳል፡-
ኢየሱስ ታዲያ ስንት ባህሪ ነበረው? ሁለት ባህሪ (አምላክ እና ሰው) ወይስ አንድ ባህሪ ብቻ? ለዚህ ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ አንድ
የነበረችውን ቤ/ክርስቲያን የምእራቡና የምስራቁ በሚል ለሁለት እንድትከፈል አድርጓታል፡፡ ሽመልስ ይፍሩ ይህን ጉዳይ አስመልከቶ ቀደም ሲል በተጠቀሰው መፅሃፋቸው ውሰጥ
የሚከተለውን ማጠቃለያ ሰጥተዋል፡-አንድ ባህሪ የሚሉት አንድ ማለትን
የሙጢኝ የሚሉት ክርስቶስን በሁለት ባህሪ ከፍለን እንዳንመለከት ካላቸው ከፍተኛ ስጋት የተነሳ ነው፡፡ ሁለት ባህሪ የሚሉትም ሁለት
ማለትን ጠበቅ የሚያደርጉት ከሁለት አንዱ መለኮት ጠቅላይ ተደርጎ የሚታሰብበትን መንገድ ለመዝጋት ነው፡፡ሆኖም በሁለቱም በኩል ያለውን
ስጋት ለማለዘብ አቅም ያለው ተዐቅቦ የሚል ቃል በሁለቱም ወገኖች የተዋህዶ ገለፃ ውስጥ መኖሩ ስጋቱን ስጋት ሆኖ እንዳይቀጥል
ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በማለት ሁለቱንም ወገኖች ሊያስታርቅ የሚችል ሃሳብ አቅርበዋል፡፡
ሌላው
ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆነውና ሳይነሳ መታለፍ የሌለበት የኬኖሲስ ንድፈ
ሃሳብ ተብሎ የሚታወቀው አመለካከት ነው፡፡ይህ አመለካከት መሰረቱን የሚያደርገው በፊሊ 2፡5-7 ያለውን ሃሳብ ነው፡፡
|
በክርስቶስ
ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።
|
|
እርሱ
በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
|
|
ነገር
ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
|
ይህ
አመለካከት በጥቅሉ ሲታይ ክርስቶስ በምድር በተመላለሰበት ጊዜ አንዳንድ የመለኮት ባህሪን እንደተወ ከላይ በተቀመጠው ጥቅስ ውስጥ
ያለውን ራሱን ባዶ አደረገ የሚለውን ሃሳብ ይጠቀማል፡፡ ይህ
አስተሳሰብን በጥልቀት ከመረመርነው ለእኛ በመስቀል ሞቶ ዋጋ የከፈለልን ሰው ብቻ ነበር ወደሚል ኑፋቄ ሊወስደን የሚችል አደገኛ
ትምህርት ነው፡፡ የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍሉን ግን በጥንቃቄ ካጠናነው በመጀመሪያ ደረጃ ሃሳቡ ስለትህትና የተፃፈ መሆኑን ማስተዋል አለብን፡፡
በመቀጠልም መለኮታዊ ባህሪን ስለመተው የሚያመላክት አንዳችም ፍንጭ እንደሌለው ማስተዋል ይኖርብናል፡፡
ይህን
ሃሳብ ለማጠቃለል ያህል ኢየሱስ ክርሰቶስ መለኮትና ሰውነት በአንድነት የተገለፁበት አንድ አካል ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህን ስንልም
መለኮትና ሰውነት ያለመዋዋጥ፣ ያለመነጣጠል፤ ያለመደበላለቅና ያለመጠፋፋት በክርስቶስ ውስጥ ተገልጠዋል ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ አሁን በክብር ነው ያለው ስንል ምን ማለታቸን ነው?
ኢየሱስ የለበሰውን ስጋ ይዞት ሄዷል? ኢየሱስ አሁን ምን አይነት ማንነት አለው?:: ኢየሱስ ስጋን ገንዘቡ ከማድረጉ በፊት የነበረውን
ማንነት እንዲሁም በምድር ሲመላለስ የነበረውን ማንነት ለመቃኘት ሞክረናል በመሆኑም ከላይ ያነሳናቸውን ጥያቄዎች አሁን ያለውን የኢየሱስን
ማንነት ለመረዳት ይረዳናል፡፡ በክብር ነው ያለው ማለት በምድር ይመላላለስበት እንደነበረው ራሱን ዝቅ አላደረገም ማለት ነው፡፡
በምድር በተመላለሰበት ጊዜ ሰዎች ሊሰድቡት ሊገርፉት እና ሊያሰቃዩት የሚችል ማንነት ነበረው፡፡ በፈቃዱ እራሱን ዝቅ አድርጎ መከራ
እና ችግር ተቀብሏል፡፡ አሁን ኢየሰሱ ገዢ፣ ፈራጅ… ነው፡፡ በታላቅ ግርማ ያለ ንጉስ ነው (ራዕ
1÷10-23)፡፡ ኢየሱስ አሁንም ፍጹም ሰው ፍጹምም አምላክ
ሆኖ ይኖራል፡፡ የለበሰውንም ስጋ አልተወውም የዩሀንስ ራዕይ ጸሀፊ የገለጠው ኢየሱስ ‹‹…እነሆም ነጭ ደመና፣ በደመናውም ላይ የሰውን
ልጅ የሚመስል ተቀምጧል በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ላይ ስለታም ማጭድ ነበረው…›› (ራዕ 14÷14)
15÷3-5
ዕብራዊያን 4÷14“
‹‹በሰማያት ያረፈ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላለን ….››ይላል ኢየሱስ በዘላለም ልጅነቱ ደግሞም
ለእኛ ካህን ሆኖ ይኖራል፡፡ አንዴ ለዘለአለም በሆነ የማማላድ ተግባሩም ስለእኛ ይማልድልናል፡፡
በመጀመሪያ ስለ ስህተት አስተምህሮዎች ከማወራታችን
በፊት ስለ ክርስቶስ አምላክነትራሱ ክርስቶስ ስለ ራሱ በመጠየቅ ከሐዋሪያው ጴጥሮስ ያገኝው መልስ እንመልከት ይህ ምላሽም ህያው የእግዚአብሔር ልጅ የሚል ሲሆን ይህ ምላሽም ጴጥሮስን ብፁ
ያስባለው መልስና የቤተ-ክርስቲያንም መሰረት የሆነውን እውነት በመቀበል በዚህ መሰረት ላይተተክለናል፡፡
እውነታው ይህ ቢሆንም በተለያዩ ዘመናት በኢየሱስ
ማንነት ላይ ብዙ የስህተት ትምህርቶች ተነስተዋል፡፡ ምላሽም ሲሰጥባቸው ኖረዋል፡፡ ኢየሱስ ሰው ብቻነው ከሚለው አንስቶ አይደለም
ኢየሱስ መለኮት ብቻ እነጂ ሰው አይደለም ለሚሉት የስህተት ትምህርቶችም ምላሾች ሲሰጡ ኖረዋል፡፡
የኢየሱስ መለኮትነትን በመካድ የተነሱ ብዙ የስህተት
ትምህርቶች ቢኖሩም የአሪዮስን ያህል ጠንካራና ቤ/ክርስቲያንን የበጠበጠ አስተምህሮ ግን አልነበረም፡፡ አሪዮስ በ275 ዓ/ም አካባቢ በሊቢያ የነበረና ከግብፅ ጳጳስ ከእስክንድሮስ ጋር
ወዳጅ የነበረ ሲሆን በማስተማር የታወቀና ከጊዜ በኋላ የክርስቶስን አምላክነት በመካድ የስህትት አስተምህሮን አስፋፍቷል፡፡ ይህን
ትምህርቱን መፅሃፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ ለማሳየት ከመ/ቅዱስ ምሳሌ 8፡22 ቆላ 1፡15 ዘዳ ምዕ6 እና የመሳሰሉትን ክፍሎች በመጠቃቀስ
በጊዜ ብዙዎችን አስቶ ነበር፡፡ በ325 ዓ/ም 318 አባቶች የተሳተፉበት የኒቂያ ጉባኤ እዲካሄድ ሆኗል፡፡ በዚህ ጉባኤም ከፍተኛ
የሆነ ክርክር ከተደረገ በኋላ የአሪዮስ አስተምህሮ ስህተት መሆኑ በተለያዩ የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች በማሳየት አባቶች ሊመልሱት ቢሞክሩም
ለመመለስ ባለማቻሉ ጉባኤው እሱን በማውገዝ የእምነት አቋም በመያዝ የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህም የእምነት አቋም በመያዝ ተጠናቋል፡፡
የሚከተለውንም አቋም አውጥቷል
"አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን
ሰማይና ምድርን በፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን
አለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን
ከብርሃን በተገኝ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኝ አምላክ
የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባህሪው ከአብ ጋር የሚስተካከል
ሁሉ በእርሱ የሆነ……
ሌላው ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ ሁለት ባህሪ ሁለት
አካል የሚል አስተምህሮ ይዞ የተነሳው ንስጥሮስ ነበር፡፡ ይህ አስተምሮ የማሪያም ልጅና የእግዚአብሔር ልጅ የሚል ነበር፡፡ ይህ
አስተምህሮም በቁስጥንጥኒያ ላይ በተጠራ ጉባኤ ተቀባይነት ሳያገኝ ንስጥሮስን በማውገዝ መደምደሚያውን ያገኝ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ
የንስጥሮስ አስተምህሮ የአሪዮስን ያህል ተፅእኖ ፈጣሪ አልነበረም፡፡
ሌላው የስህተት ትምህርት በሰባሊዮስ የተጀመረ
ሲሆን የአመለካከቱ አራማጆችም ሰባሊዮሳውያን ይባላሉ፡፡ አንዱ እግዚአብሔር በሶስት የተለያዩ ጊዜያት በሶስት የተለያዩ ማንነቶች
ተገልጧል የሚል ነው፡፡ ይህም ማለት በአባቶቻችን ጊዜ ( በብሉይ ኪዳን) "አብ" ፤ በአዲስ ኪዳን ዘመን "ወልድ" እና በቤተ ክርስቲያን ዘመን "መንፈስ
ቅዱስ" በመሆን ተገለጠ የሚል ሲሆን ይህም አስተምህሮ ኦንሊ ጂሰስ በመባል የሚታወቀው የእምነት ቡድን አቋም በመሆን እስካሁን
ድረስ የሚገኝ ሲሆን ምንም አይነት ጠንካራ የመ/ቅዱስ ማስረጃ የሌለው አስተምህሮ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ የክርስቶስን ሰውነት
በመካድ የተነሳው የአውጣኬ አስተምህሮ ነው፡፡ የንስጥሮስን አስተምህሮ ለመከላከል በሚል መለኮት ስጋን ውጦታል ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ
መለኮት ብቻ ነውየሚልና የመዋዋጥ ትምህርትን ያዘለ ነው፡፡ ይህም ትምህርት በወቅቱ በነበሩ የቤ/ክርስቲያን አባቶች ተገቢው ምላሽ
ተሰጥቶታል፡፡
እንግዲህ በጥቂቱ ዋና ዋናዎቹ የክህደት
ትምህርቶች እነዚህ ናቸው እንጂ ሌሎች አስተምህሮዎች አልነበሩም ማለት አይደለም፡፡ ቢሆንም ለያንዳንዱ የስህተት ትምህርት ትምህርቶቹ
በተነሱበት ወቅት በነበሩ የቤ/ክርስቲያን አባቶች ተገቢው ምላሽ በመሰጠቱ አሁን ያለንበትን ጠንካራ የስነ-ክርስቶስ አሰተምህሮ ለማግኝት
በቅተናል፡፡
by: Yosef Masresha,