የሰው ተፈጥሮን አስመልክቶ
ሶስት የተለያዩ አመለካከቶች አሉ፡፡ እነርሱ መሰረታቸው የሚያደርጉት በስጋ፣ በመንፈስ እና በነፍስ ላይ ነው፡፡ እንደየአመለካከቶቹ
ሰው አንድ፣ ሁለት ወይም ሶስት ክፍለች አሉት ብለው የከራከራሉ፡፡
በዚህ አጭር ፅሁፍ ውስጥ
ለአመለካከቶቹ መፈጠር ዋነኛ ምክኒያት የሆኑትን ቃላቶች በመጀመሪያ በመተርጎም ሶስቱንም አመለካከቶች ከተመለከትን በኋላ በመጨረሻ
የግል አመለካከቴን በማጠቃለያ ላይ ለማስፈር እሞክራለሁ፡፡
I.
ስጋ፣ ነፍስ እና መንፈስ
ስጋ፡- በአይን የሚታይ እና የሚዳሰስ የሰው ክፍል ሲሆን ስጋ፣ ደም፣አጥንት፣የተለያዩ ብልቶችን
እና ህዋሳትን ያመለክታል
- ስጋ ብለን የምንጠራው በዘፍ 2፡7 መሰረት ከአፈር የተበጀውን
አካል ነው፡፡
- ሰው ሲሞትም ተለይቶ አፈር የሚሆነው ይህ አካሉ ነው[ዘፍ 3፡19
፣ መክ 12፡7]
ነፍስ፡- ነፍስ ብለን የምንጠራው ቁሳዊ ያልሆነውንና የማይሞተውን የሰው ክፍል ነው፡፡
- ይህ ክፍል አእምሮ፣ ስሜት፣ ፈቃድ እና የመሳሰሉትን የማይታዩ
የሰው ባህሪያት ይወክላል፡፡
- ይህ የሰብእና ክፍል አንዳንድ ጊዜ ሰውን እራሱን ወክሎ የቀርባል
(ሐዋ፡2፡41)
መንፈስ፡- ማለት በሰው
ስብህና ውስጥ ያለ ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር የምንገናኝበት ቁሳዊ ያልሆነ የስህብናችን ክፍል ነው፡፡ (ዮሐ 4፡24)
መንፈስ የሚወክለው የማይታየውን እና የማይዳሰሰውን ቁሳዊ ያልሆነ የስህብናችን ክፍል ብቻ ነው፡፡
II. የሰው የስህብና ክፍለ አካላትን አስመልክቶ ያሉ አመለካከቶች
1.
ባለ አንድ ስብህና ክፍለ አካል
/Monochotomy /
[ሰው=ስጋ/ነፍስ/መንፈስ]
ይህ አመለካከት እምብዛም
ብዙ ተከታይ ያለው አመለካከት አይደለም፡፡
የዚህ አመለካከት አራማጆች
ሰው ተነጣጥሎ ወይም ተከፋፍሎ ሊታይ የማይችል ፍጥረተ ነው ()
ብለው ያምናሉ በዚህ
አመለካከት መሠረት ሰው የምንለው ፍጥረት በስጋ በነፍስ ወይም በመንፈስ መከፋፈል አይቻልም፡፡
2.
ባለ ሁለት ስብህና ክፍለ አካላት/Dichotomy/
[ሰው=ስጋ+ነፍስ/መንፈስ]
ይህ
አመለካከት የሰው ማንነት በሚታይ አና በማይታይ አካል የተገነባ ነው የሚል ሲሆን የዚህ አመለካከት አራማጆች በሰው የሚታይ አካል
ስጋ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ የማይታየው የሰው ክፍል ደግሞ ነፍስ ወይም መንፈስ ብለን ልንጠራው እንችላለን ይላሉ፡፡
ይህ
አመለካከትን የሚከተሉ ሰዎች አመለካከታቸው ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ከመፅሐፍ ቅዱስ ስጋን እና መንፈስን ወይም ነፍስን የሚጠቅሱ
ክፍሎችን የጠቅሳሉ፡፡
ለምሳሌ፡-
ስጋ እና ነፍስ- ማቴ፡6፡25 ፣ማቴ፡10፡28
- ስጋ እና መንፈስ- ማቴ፡26፡41፣ ሮሜ፡8፡10
የዝህ
አመለካከት ዋና መገለጫ ነፍስ አና መንፈስ አይነጣጠሉም ወይም አንድ ናቸው የሚል ሲሆን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥም ሁለቱ ቃላት በመተካካት
ተጠቅሰዋል ማለቱ ነው፡፡
3. ባለ ሠስት ስብህና ክፍለ አካላት/trichotomy/
[ሰው=ስጋ+ነፍስ+መንፈስ]
ይህ
አመለካከት መሰረቱን የሚያደርገው ነፍስ እና መንፈስ በመለየት ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ አመለካከት መሰረት ሰው ማለት የስጋ የነፍስና
የመንፈስ የ ጋራ ውጤት ነው፡፡
የዚህ
አመለካከት አራማጆች Dichotomy የሚለዩት ነፍስ እና መንፈስን ነጣጥለው ስለሚመለከቱ ነው፡፡
በዚህ
አመለካከት መሰረት በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነፍስ እን መንፈስ በመተካካት የተቀመጡ ሳይሆን እንደ ሁለት የተለያዩ ክፍሎች ይጠቅሷቸዋል፡፡
ስለዚህ ለDichotomy
የሚጠቀሱ ጥቅሶችን እና ሁለት ተጨማሪ ጥቅሶችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ይጠቀማሉ፡፡ [1ተሰ፡5፡17-23፣ እብ፡4፡12]
III.
ማጠቃለያ
የሰው
ስብእና Monochotomy ፣Dichotomy ወይም richotomy ስለመሆኑ ምንም አይነት ግልፅ ማስረጀ አይሰጠንም፡፡ ነገር
ግን በመፅሐፍ ቅዱሳችን ብዙ ቦታዎች ስጋ፣ መንፈስ አና ነፍስ በተደጋጋሚ ተጠቅሰዋል፡፡ እንዚህም በመ/ቅዱስ የተጠቀሱ ጥቅሶችን
በመገጣጠም የተለዩ አመለካከቶች ተነስተዋል፡፡ ነገር ግን ሦስቱም አመለካከቶች ላይ ጥያቄወች ይነሳሉ፡፡
ለምሳሌ፡-
ባለ አሀዳዊዎቹ ከመ/ቅዱስ አንፃር ይህንን አሳባቸውን ለማስረዳት ይቸገራሉ፡፡
- ባለ ሁለትዮሾቹ ደግሞ ስለ ነፍስ እና መንፈስ አንድነት አጥጋቢ
መልስ መስጠት ይሳናቸዋል፡፡
- ባለ ሦስትዮሾቹ ደግሞ ሦስተኛ ብለው የሚጨምሩትን መንፈስ መቼ
ወደ ሰው ስብእና እንደገባ ወይም እንደተፈጠረ ለማስረዳት ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡
በእኔ
አመለካከት ስለ ሰው ተፈጥሮ ከመወሰናችን በፊት በመ/ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱትን ጥቅሶች መመርመር እጅግ አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ስለ
ነፍስ- ማቴ6፡25፣ ማቴ10፡28፣ መክ፡12፡7 ፣ሉቃ26፡41 ፣ራዕ፡6፡9 ፣መዝ35፡3 ፣ ማቴ፡1፡46 ፣ሀዋ፡2፡34 ፣1ቆሮ፡7፡34
ከላይ
የተጠቀሱትን ጥቅሶች እና ሌሎችም ጥቅሶች በምንመለከትበት ጊዜ ስለ ነፍስ የሚነግረን ነፍስ የማትሞት እንደሆነች፣ በመብል እና በመጠጥ
የምትደሰት፣ አምላኳን የምታከብር እና ልትቀደስ የሚገባት መሆኗን ነው፡፡
ስነ-መንፈስ-
ሮሜ8፡10፣1ቆሮ፡5፡3 ፣2ቆሮ፡7፡1 ፣ማቴ፡26፡41 ፣ ማቴ1፡47 ፣ሮሜ8፡6
ከላይ
የተጠቀሱትን ጥቅሶች ስንመለከት መንፈስ በፅድቅ ምክንያት ህያው የሚሆን፣ ከወንድሞች ጋር ህብረት የምናደርግበት፣ በሃጥያት የሚረክስ
የእግዚአብሔር ፈቃድን ለመፈፀም የሚዘጋጅ፣ በእግዚአብሔር አሴት የሚያደርግ እና ከመንፈስ ጋር ህብረት ያለው መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡
ስለዚህ
እነዚህን ሁሉ ጥቅሶች ከመረመርን በኃላ ስለ ሰው አፈጣጠር በዘፍ2፡7 የተፃፈውን መመልከቱ ተገቢ የሆናል፡፡
ዘፍ2፡7
1. ከምድር አፈር አበጀው
2. የሂወት እስትንፋስ እፍ አለበት
3. ሂያው ነፍስ ያለው ሆነ
ይህ
የመ/ቅዱስ ክፍልን 1ኛውን ብናየው ሁላችንንም ያስማማናል ነገር ግን ሁለተኛውን መንፈስ ሦስተኛውን ደግሞ ነፍስ ብሎ መተርጐሙ ግን
ተገቢ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም እፍ የተባወበት እስትንፋስ ነፍስ አደረገው እንጂ መንፈሱ ነፍስን አመጣ ብሎ መደምደም ከባድ ነው፡፡
ምክንያቱም ይህ ማለት መንፈስ ከለለ ነፍስ የለም ወደሚል ድምዳሜ ሊያመራን ይችላላ፡፡
በሌላ
በኩል ደግሞ ነፍስ አና መንፈስን ጨፍልቆ ማየቱ ተገቢ አይሆንም ምክንያቱም ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች ሁለቱም ሟች እንዳልሆነ ብናይም
መንፈስ ግን የተጠቀሰው በተለየ ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የምናደርግበት መሆኑ ነው በተጨማሪም መ/ቅዱሳችን ሦስት ቦታ
ነፍስ እና መንፈስ ተለያይተው በአንድ ጥቅስ ተፅፈዋል የመጀመሪያው
1.
ሉቃ፡1፡46-47-
-ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች
- መንፈሴ በአምላኬ በመዳሊቴ አሴት ታደርጋለች
ይህም
ጥቅስ የሚያረጋግጥልን መንፈስ ለጌታ የቀረበች መሆኗን ነው፡፡
2.
1ተሰ፡5፡23
- -… በመንፈሳቹም ነፍሳቹም ስጋቹም…
- በዚህ ጥቅስም የምንረዳው ሦስት የተለያዩ የሰው ስብእና ክፍለ
አካላትን ነው፡፡
3.
እብ፡4፡12
- - … ነፍስ እና መንፈስን…
- ይህ ጥቅስ የሚያመለክተን ነፍስ እና መንፈስ በአጅጉ የተቀራረቡ
መሆናቸውን ሲሆን ነገር ግን ፍፁም የተቀላቀሉ አለመሆናቸውንም ያስረዳል፡፡
ከላይ
የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ሁሉ በመመልከት የሰው የስእብና ክፍለ አካላት ስጋ፣ነፍስእና መንፈስ ሲሆኑ ነፍስ እና መንፈስ ከአካላዊ
የህይወት ጊዜ ያለፈ የህይወት ቆያታ ያላቸው መሆኑ ነው፡፡
በተለይ
እብ፡4፡12 በመመልከት 1ኛ. በነፍስ እና በመንፈስ መካከል የሚለይ ነጥብ መኖሩን
2ኛ. ይህን የመለያ ነጥብም በእግዚአብሔር
ወይም በቃሉ ብቻ የሚለይ መሆኑን መደምደም ይቻላል፡፡
ይህ
ማለት ግን ሁለትዮሽ አመለካከት ተከታዮች ስህተተኛ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ መ/ቅዱስ በግልፅ ባስቀመጠው ጉዳይ ላይም ይህን ያህል
ትኩረት ማድረጉም አላስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ከሁሉ ይበልጥ ግን ሊተኮርበት የሚገባው “መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም፣ ስጋችሁም ጌታችን
እየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈፅሞ ይጠበቁ፡፡" የሚለው የተከበረ የቃሉ ማሳሰቢያ ሊሆን ይገባዋል፡፡
1 comment:
ጥሩ ፅሁፍ ናት…የመንፈስና የነፍስን ልዩነትን ካመንክ ለምን አቋምህ ከመግቢያው ጀምሮ trichomy እንደሆነ አለመለከትህም? የሰጠሃቸው ጥቅሶች ሁሉ trichomy ሦስትዮሽን በሚገባ የሚደግፉ ናቸው። እንደመረመርኩትም ትክክለኛው መረዳት ያ ይመስለኛል። በርታ brother Jossy!
Post a Comment